አማርኛ | English
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ት/ቤት
                                                       
ታሪካችን
በ1970 ዓ/ም እንደ ኢትዮጵያዊያን አቆጣጠር በአቶ አለባቸው አድማሳቸው እና በባለቤታቸው በወ/ሮ ማርታ ወርቁ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ለማስተማር በሩን ከከፈተ ጀምሮ ኢኤልሲሲ አነሆ አርባ አመታትን ይዟል ። በዚህ ሁሉ ግዜ ውስጥ ያለው ታሪካችን ማስተማር እና ማስተማር ብቻ ነው።
አቶ አለባቸው በህይወት በኖረበት ዘመናት ከአስር ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን በጣም ጥሩ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተጠቃሚ አድርገዋል ።
ልጁም ወ/ሮ ኖዌል አለባቸው ለአስራ አምስት አመታት በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ በማስተማር የቆየች ሲሆን፣ ከዛ በፊትም ያሉትን ሦስት ዓመታት በአስጠኚነት ስትሰራ ቆይታለች።
ኢኤልሲሲ ከተከፈተ ጀምሮ ለሠላሳ ዓመታት “የእንግሊዝኛ ቋንቋ ት/ቤት” በመባል ይጠራ የነበረ ሲሆን፣ በኢትዮጵያም የመጀመሪያው የግል የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሰልጠኛ ነው።
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ጥቅም ከኢንተርኔት መስፋፋት ጋር ተያይዞ ይሄ ነው ብሎ ለመገደብ ከሚቻለው በላይ ሆኗል ፤ ይህንንም በመረዳት ት/ቤታችን እንግሊዝኛ የኢትዮጵያ ሁለተኛ ቋንቋ እንዲሆን ሲጥር ቆይቷል። በዚህም ዓላማችን ተበረታትተው በርካታ የቋንቋ ማሠልጠኛ ማዕከላት የተቋቋሙ ቢሆንም ፡ ቁጥራቸው በቂ አይደለም። አሁንም ቢሆን ብቃቱ ያላችሁ ሰዎች ተጨማሪ ማዕከላትን ክፈቱ እንላለን።

ይሄ ታሪካችንም ነው የወደፊት ዓላማችንም ነው።
ዋናው ህልማችን ጠቃሚ የሆነውን የእንግሊዝኛ ቋንቋን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ቋንቋ ማድረግ ፣ ኢትዮጵያም ቅኝ ሳትገዛ የሌላ ሀገር ቋንቋን በብቃት የምትጠቀም ስትሆን ማየት ነው።
ስልክ : +251 92 934 7160 ወይም +251 91 045 6695 ኢሜል : noelawise@gmail.com