አማርኛ | English
ኢ ኤል ሲ ሲ ፦ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማዕከል
                                                       
ስልክ : +251 92 934 7160 ወይም +251 91 045 6695 ኢሜል : noelawise@gmail.com

የእንግሊዝኛ ቋንቋ በአሁኑ ግዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዋናነት ተመራጭነት ያለው ነው ። የትም ሀገር ቢሄዱ ፣ ምንም አይነት አለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ቢሰሩ ፣ የትኛውንም ስራ በብቃት ለማከናወን እንግሊዝኛ ቋንቋ ወሳኝ ነው።

በአርባ አመት የእንግሊዝኛ ቋንቋ የማስተማር ሂደት ውስጥ ፡ ኢ ኤል ሲ ሲ ከሃያ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን እንግሊዚኛ ቋንቋ በብቃት እና በጥራት እንዲጠቀሙ አድርጓል ።

ሀሳባችንን በማህበራዊ ገጽ ላይ በጥራት ለማንጸባረቅ እንግሊዝኛችንን እናዘምን

አሁን ከሚገኙበት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ደረጃ ከሦስት እስከ ስድስት ወር ባልበለጠ ግዜ ውስጥ ብቁ የሚሆኑ ሲሆን ፤ ይህንንም ለማድረግ ምርጥ አስተማሪዎች ፣ ከግዜው ጋር የሚሄዱ የማስተማሪ መሳሪያዎች ፣ እንዲሁም ዘመናዊ የማስተማሪያ መጽሐፍት በመጠቀም ላይ ነን። በዚህ አካሄድ በርካታ ኢትዮጵያውያንን በጣም አሪፍ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተጠቃሚ ለማድረግ አስበናል።

ሙያተኞቹ ጋር ይቀላቀሉ።
ቋንቋ እንደ ሙያ አራት ነገሮችን ብቻ ማዳበር ነው ፡ መስማት ፣ መናገር ፣ ማንበብ ፣ መጻፍ ፡ ከዚህ ያለፈ ምንም ተጨማሪ ነገር የለውም።
የተለየ የሰዋሰው ትምህርት አንሰጥም!

በዚህ ድረ ገጽ ላይ በመመዝገብ ይዘምኑ

መመዝገቢያ ክፍል


ምንም ዓይነት ጥያቄ ካለዎት ይላኩልን ፡ መልስ መስጠት ደስታችን ነው።የት ነው የምንገኘው?
ፒያሳ ፦ ከሲኒማ አምፒር ፊት ለፊት በሚገኘው ወደሠራተኛ ሰፈር መውረጃ አስፋልት ይዘው ጉዞ እንደጀመሩ በቀኞ በኩል አራት ቆንጆ ቆንጆ ሱቆችን ያልፋሉ። ከአራተኛው መደብር ቀጥሎ የትምህርት ቤታችን የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ይገኛል ፡ እዚህ ውስጥ ታሪካዊው የልዕልት ተናኘወርቅ ህንፃ የሚገኝ ሲሆን ፡ ትምህርት ቤታችን አንደኛ ፎቅ ላይ ነው።